Duty-Free Notes

ጠቅልለው ወደ ሀገር ቤት ሲገቡ ቀረጥና ታክስ ከፍለው እቃዎች ለማስገባት ለሚፈልጉ አመልካቾች

  • እባክዎ አገልግሎቱን አዘጋጅተን እንድንሰጥዎ በጥንቃቄ አንብበው አስፈላጊውን ማስረጃዎች ከነ ፎቶ ኮፒያቸው አያይዘው ይላኩ።

  • አገልግሎቱን ለመጠየቅ አንድ አመትና ከዚያ በላይ በውጭ አገር የኖሩ መሆን ይኖርብዎታል።

  • በአምስት አመት ጊዜ ውስጥ ከአንድ ጊዜ በላይ አገልግሎቱን መጠየቅ አይችሉም።

አገልግሎቱ ለማግኘት የሚከተሉትን መስፈርቶች ያሟሉ

1)

አንድ አመትና ከዚያ በላይ በውጭ አገር መቆየትዎን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ፣ የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ እና ሌላ ማስረጃ ማቅረብ

2)

ኢትዮጵያዊ ከሆኑ አገልግሎቱ ያላበቃ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም በትውልድ ኢትዮጵያዊ ከሆኑ አገልግሎቱ ያላበቃ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ በሁለት ኮፒ

3)

የመኖሪያ ፈቃድ

4)

መጠየቂያ ቅጽ መሙላት (ይህን በመጫን ቅጹን ያውርዱ)

5)

ማመልከቻ

6)

የሚያስገቡት እቃዎች ዝርዝር (ይህን በመጫን ቅጹን ያውርዱ)
     7) ከተገዛበት አገር የተረጋገጠ መኪና (የኤሌክትሪክ ወይም በሁለቱም የሚሰራ) የተገዛበት ደረሰኝ /Commercial Invoice/
   

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook