Power of Attorney

የውክልና ስልጣን አገልግሎት

እርስዎን ወክሎ በኢትዮጵያ ውስጥ ጉዳዮችን የሚከታተል ሰው(ዎች) ወይም ተወካይ ለመሾም ከፈለጉ የውክልና ስልጣን ያስፈልግዎታል።

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስር በዓለም ዙሪያ በኢምባሲና ቆንጽላ ጽህፈት ቤት በኩል የሚሰጡ የውክልና ስልጣን አገልግሎት የኦንላይን አገልግሎት መስጫ አማራጮችን አቅርቧል። በመሆኑም የኦንላይን አገልግሎትን https://digitalmofa.com ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

የዲጂታል የኦንላይን ውክልና መተግበሪያን በ iOS እና Android ማውረድ ይችላሉ።

በኤምባሲው ቆንስላ ፅ/ቤት አገልግሎቱን ማግኘት ለምትፈልጉ:-

ለኢትዮጵያዊያን

      • ፓስፖርት ኦርጅናልና ኮፒ (የአገልግሎት ጊዜው ያላለፈበት ቢያንስ የ6 ወር ጊዜ ያለው)
      • የመኖርያ ፍቃድ ኦርጅናልና ኮፒ
      • ማመልከቻ
      • የተወካይ የቀበሌ መታወቂያ ኮፒ (የተወካይ ሙሉ ስምና አድራሻ የሚታይ)
      • የአገልግሎት ክፍያ 38 ዶላር

ለትውልድ ኢትዮጵያዊያን

      • ፓስፖርት ኦርጅናልና ኮፒ
      •  የትውልድ ኢትዮጵያ መታወቂያ ኦርጅናልና ኮፒ (የአገልግሎት ጊዜው ያላለፈበት ቢያንስ የ6 ወር ጊዜ ያለው)
      • ማመልከቻ
      • የተወካይ የቀበሌ መታወቂያ ኮፒ (የተወካይ ሙሉ ስምና አድራሻ የሚታይ)
      • የአገልግሎት ክፍያ 38 ዶላር

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook